Tuesday, October 8, 2024
spot_img

የተከዜ ድልድይ ዳግም መጠገኑ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― ከሁለት ወራት በፊት መፍረሱ ተነግሮ የነበረው የተከዜ ድልድይ ዳግም መጠገኑን በሕወሃት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ሠፍሯል።

በትግራይ ክልል የሚገኘው እና ጎንደርን ከሽሬ የሚያገናኘው ግዙፉ የተከዜ ድልድይ ከ100 ሜትር በላይ ርዝማኔ አለው የሚባልለት ነው።

አሁን እንደተጠገነ የተነገረለት ይኸው ድልድይ በፈረሰበት ወቅት ማን አፈረሰው የሚለው አነጋግሮ ነበር።

መንግስት “ሕወሓት ሆን ብሎ ነው የተከዜ ድልድይን ያፈረሰው” በሚል ሲወነጅል፣ ሕወሃት በተመሳሳይ መንግስትና አብረውት ተሰልፈዋል የሚላቸውን ኃይሎች ሲከስ ቆይቷል። የተመድ የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ በወቅቱ የአማራ ልዩ ኃይል ድልድዩን አፍርሶታል የሚል መረጃ ደርሶኛል ብሎ ነበር።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img