Friday, October 18, 2024
spot_img

በአልጀርስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊዘጋ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― በአልጀሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ኢምባሲ ከመስከረም 30፣ 202014 ጀምሮ ይዘጋል፡፡

ኢምባሲው የሚዘጋው የኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ጉዳት ምክንያት በተፈጠረው የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እንደገና ለማደራጀት መንግስት በመወሰኑ እንደሆነም ኢምባሲው አስታውቋል። ይሁንና ኢምባሲው የሚዘጋው በጊዜያዊነት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተጎዳው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሲስተካከል ኢምባሲው ዳግም እንደሚከፈትም ተገልጿል።

እስከዚያው ድረስም የሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ስራዎች ከአዲስ አበባ እንደሚከናወኑም ተገልጿል።

የኢምባሲው መዘጋት በኢትዮጵያ እና አልጀሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጎን እንደሌለም ኢምባሲው በመግለጫው ገልጿል።

ከሁለት ወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትይጵያ በተለያዩ ሀገራት የከፈተቻቸውን ኢምባሲዎች የመቀነስ እቅድ አንዳላት መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img