Friday, October 18, 2024
spot_img

ሳፋሪኮም የሥራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ለመንግሥት ማብራሪያ ሰጠ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም፣ የሥራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዋና ሥራ አስፈጻሚው ፒተር ንዴግዋ የተማራው የሳፋሪኮም ልኡክ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እና ሚኒስቴር ዲኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚሁ በገንዘብ ሚኒስቴር ፍሬያማ በተባለው ውይይት ወቅት የሳፋሪኮም ኃላፊዎች ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየሠራ የሚገኘውን እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡

ከመንገስት የሥራ ኃላፊዎቹ መካከል የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ መንግስት በቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች ጥራት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ለሳፋሪኮም ድጋፍ እንደሚደርግም ገልጸዋል መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ሳፋሪኮም የሚመራውና አምስት ኩባንያዎች እና ተቋማትን ያካተተው ‹‹ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ›› የተሰኘው ጥምረት የሚያቋቁመው ኩባንያ፤ በኢትዮጵያ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የማቅረብ ስራውን በጥር 2014 ለመጀመር እንዳቀደ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ አዲሱ ኩባንያ አሁን በሀገሪቱ በብቸኝነት የቴሌኮም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮምን የሚገዳደር መሆኑ ተነግሮለታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img