Sunday, September 22, 2024
spot_img

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን አምስት ሚሊሺያዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ስር ወዳለችው ቡለን ወረዳ፤ ዛሬ ረፋዱን በባጃጅ ሲጓዙ የነበሩ አምስት ሚሊሺያዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የጉሙዝ ታጣቂዎች አምስት ሚሊሺያዎችን መግደላቸውን አረጋግጠዋል።

ሚሊሺያዎቹ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው “ለአካባቢ መጠበቂያ የሚሆን [ትጥቅ] ሊታጠቁ ወደ ከተማው ማዕከል በመጓዝ ላይ እያሉ” መሆኑን አቶ አብዮት ገልጸዋል። በመተከል ዞን ከምትገኘው ዶቤ ቀበሌ እንደተነሱ የተነገረላቸው ሚሊሺያዎች፤ ወደ ቡለን ከተማ ሲጓዙ የነበረው በሶስት ባጃጆች ተሳፍረው ነበር ተብሏል።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የሰነዘሩት በአንደኛው ባጃጅ ውስጥ በነበሩ ሰባት ሚሊሺያዎች ላይ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img