Friday, October 18, 2024
spot_img

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት ጋር በስልክ መከሩ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ዑመር ጉሌድ ጋር በስልክ መወያየታቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

መሪዎቹ በውይይታቸው የሁለቱን አገራት ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውን የገለጸው ኤምባሲው፣ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣናዊ ጉዳዮች መምከራቸውንም ነው ያመለከተው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው እሑድ በተመሳሳይ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ ወደሚገኙት ኡጋንዳ እና ሩዋንዳ በማቅናት ከመሪዎችቻቸው ዩዌሪ ሙሴቪኒ እና ፖል ካጋሜ ጋር መምከራቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img