Friday, October 18, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የአቪዬሽን መዳረሻ ማዕከል የሚያደርገውን ስምምነት ከቦይንግ ጋር ተፈራረመ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የቦይንግ ኩባንያ ኢትዮጵያን በአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል ለማድረግ ስትራቴጂያዊ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል።

ሁለቱ አካላት በአቪዬሽን ውስጥ ያላቸውን የሰባ ዓመት የወዳጅነት ታሪክ በማስመልከት የመግባቢያ ስምምነቱ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአቪዬሽን ማዕከል እንዲሆን የማድረግ ዓላማን የያዘ ነው።

ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የላቀ የአቪዬሽን ሥልጠና፣ የትምህርት አጋርነት እና የአመራር ልማት ስራዎችን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከግብ ለማድረስ ያለመ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ተቋሙ የሰው ኃይል ፍላጎቶችን ለማሟላት ልዩ የትምህርት እና የልማት ፕሮግራሞችን ለመፍጠር ከፍተኛ ብቃት ካላቸው የትምህርት ተቋማት እና ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪ አጋሮች ጋር በመተባበር እንደሚሰራ ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img