Sunday, September 22, 2024
spot_img

ሕወሓት የአፍሪካ ኅብረትን በወገንተኝነት ከሰሰ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ መሾሙን ተከትሎ ሕወሓት ሕብረቱን በወገንተኝነት ከሰሰ።

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ድርድር እንዲደረግና ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ የተለያዩ ወገኖች ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ትግራይ ክልል ውስጥ ተቀስቅሶ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ከሰኔ ወር ማብቂያ ወዲህ ወደ አፋርና አማራ ክልሎች ተስፋፍቷል።

ባለፈው ሳምንት አህጉራዊው ድርጅት የአፍሪካ ሕብረት ለጦርነቱ መፍትሔ ለመፈለግ እንዲራዳው የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሌሴጉን ኦባሳንጆን የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው በሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ተሹመዋል።

ነገር ግን ይህን በቀጠናው ሰላም፣ ደኅንነትና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም የፖለቲካ ውይይትን ለማበረታታት የሚያደርገው ጥረት ያግዛል ተባለው የአፍሪካ ህብረት ሹመትን ተከትሎ በሕብረቱ አቋም ላይ ከህወሓት በኩል ጥያቄን አስከትሏል።

ሕብረቱ ኦሉሴጎን ኦባሳንጆን እንደ አሸማጋይ መሾሙን ካሳወቀ ከቀናት በኋላ የሕወሓት ቡድን የአፍሪካ ሕብረትን በወገንተኝነት በመክሰስ ጥያቄ አንስቷል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ የአፍሪካ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር መወገኑን በመግለጽ ባለፉት ወራት የቆየውን ግጭት ተገቢውን ትኩረት አልሰጠውም ሲሉ ከሰዋል።

አቶ ጌታቸው በትዊተር ላይ እንዳሰፈሩት ሕወሓት አሸማጋይ መሰየሙን እንደማይቃወም ያመለከቱ ቢሆንም፣ ይህ ተልዕኮ ይሳካል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

መንግስት በሕዘዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ከተሰየመው ከህወሓት ጋር ምንም አይነት ድርድር እንደማይኖር ማሳወቁ ይታወሳል።

በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው ተሰየሙት ኦባሳንጆ ቀዳሚ ሥራ ለወራት የዘለቀውና በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img