Thursday, October 17, 2024
spot_img

አገራዊ ፈተናዎችን ለመወጣት የ‹ዱዓ› እና ‹ሰደቃ› ጥሪ ቀረበ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አገሪቱ ላይ ከውጭና ከውስጥ ተደቅኗል ያለውን አገራዊ ፈተና በድል ለመወጣት ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም ከነገ ጀምሮ በየመስጊዱ ዱዓ እና ሰደቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የምክር ቤቱ የዑለማ ምክር ቤት ሰብሳቢ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ‹‹በአገራችን ላይ ያንዣበበውን መጥፎ ደመና አላህ እንዲያነሳልን ዱዓ እና ሰደቃ እንዲደረግ›› ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም የመስጊድ አሰጋጆች፣ ለሰላት ጥሪ የሚያደርጉ ወይም ሙአዚኖች እና የሚመለከታቸው ሁሉ በየተመቻቸው ቀንና ሰዓት ወንድ ሴት፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ሀብታም ድሃ፣ ሕፃን አዋቂ ሳይባል በጋራ ስለ ኢትዮጵያ ሠላም ዱዓ እንዲደረግ ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ተግባራዊነቱም ከነገ ነሐሴ 25 ጀምሮ ችግሩ እስኪነሳ ጸሎቱ ቢቀጥል ጥሩ ይሆናል ማለታቸውን ዋልታ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img