Thursday, October 17, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐብት ከ1 ትሪሊዮን ብር ተሻገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የኢትዮያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሐብት ከ1 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልጧል፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የባንኩ ሐብት ከ1 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የ2013 በጀት ዓመት መጣናቀቂያ ድረስ መሆኑን ተናገረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝደንት የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ ባንኩ 300 ሚሊዮን ብርና ሠራተኛው ደግሞ 500 ሚሊዮን ብር በድምሩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img