Friday, November 22, 2024
spot_img

ኦነግ በኢሰመኮ ሪፖርቶች ላይ ቅሬታውን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 22፣ 2013 ― የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣቸው ሪፖርቶች ላይ ቅሬታ እንዳለው አሳውቋል፡፡

ፓርቲው በጉዳዩ ላይ መግለጫ ገለልተኛ እንዲሆን የሚታመነው የመብቶች ተቋም፣ በተደጋጋሚ ባወጣቸው ሪፖርቶች ላይ ወገንተኛ እና የፖለቲካ አላማ ያነገቡ ሪፖርቶችን ሲያወጣ ታዝቤያለሁ ብሏል፡፡

በኦነግ ከመንግስት ጋር ግንኙነት አለው የተባለው ኢሰመኮ፣ ባወጣቸው ሪፖርቶች በአማራ ክልል ያወጣቸው ሪፖርቶች ከሌሎቹ ማለትም ፓርቲ ከጠቀሳቸው የኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ትግራይ አካባቢዎች ወገንተኝነት ያመጣው ልዩነት ታዝቤያለሁ ነው ያለው፡፡

እንደ ፓርቲው ከሆነ በቅርቡ ተመልክቻቸዋለሁ ያላቸው የኮሚሽኑ ሪፖርቶች ከመንግስት ጋር በመመካከር የተሠሩ ናቸው ያለ ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የተደረገው የኮሚሽኑ ምርመራም እውነተኞቹን ተጎጂዎች ያላካተተ መሆኑን ገልጧል፡፡

የኮሚሽኑን ሪፖርት በመረጃ ማነስ፣ ርትአዊ እና ሙያዊ ባለመሆን የከሰሰው ኦነግ፣ ሪፖርቶቹን ሕብረተሰቡን አሳሳች ናቸው በማለት፣ የኮሚሽኑን ዋና ኃላፊ እና ባልደረቦቻቸውን ሆነ ብለው ፖለቲካ እና ብሔር ያጠላበት ሪፖርት ያወጣሉ ሲል ወንጅሏል፡፡

በማሳያነት ከሰሞኑ በምሥራቅ ወለጋ ደርሷል የተባለውን የንጹሐን ግድያ ሪፖርት የጠቀሰው ኦነግ፣ በአካባቢው የተፈጠረውን ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img