Monday, October 7, 2024
spot_img

ሕወሓት ለትግራዩ ጦርነት በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ፍላጎቱ መሆኑን ለተመድ በጻፈው ደብዳቤ መግለጹ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 22፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ሊቀመንበሩ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ለዘጠኝ ወራት የቆየው ጦርነት «በውይይት እንዲያበቃ» ፍላጎት ማሳየታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ የዜና ምንጭ ዘግቧል፡፡

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተላከ እና የዜና ተቋሙ ተመልክቼዋለሁ ባለው ደብዳቤ ሕወሓት «ገለልተኛ አደራዳሪ» መኖሩን እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን ጠቅሷል። ሆኖም ይኸው ደብዳቤ የአፍሪካ ኅብረት «ለጦርነቱ ማንኛውንም መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም» የሚል ሐሳብ ማስፈሩን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ሕወሓት እምነት ያጣበት የአፍሪካ ኅብረት ኦሉሴጎ ኦባሳንጆን የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው አድርጎ መሾሙን ከትላናት በስትያ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ የአፍሪቃ ኅብረት በድረ ገጹ ባሳራጨዉ ዘገባ እንዳለው ኦባሳንጆ፣ በአፍሪቃ ቀንድ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ከሁሉም ወገኖች ጋር ይነጋገራሉ።

ከትላንት በስትያ ሐሙስ መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ሥዩም በሰጡት መግለጫ ወቅት መንግስት ሊያካሄድ እንደሆነ በሚነገረው ብሔራዊ ውይይት ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ተሳታፊ ይሆናሉ ወይ ተብለው ተጠይቀው የነበረ ሲሆን፣ ቃል አቀባዩዋ «ማንኛውም ሕጋዊ የሆነ አካል በውይይቱ ተሳታፊ እንደሚሆን» መልሰዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊጠናቀቅ ባለው በዚህ ዓመት ሁለቱንም ቡድኖች በሽብረተኝነት መፈረጁ የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img