Thursday, October 17, 2024
spot_img

በእስር ላይ የነበሩ 100 ኢትዮጵያውን ወደ አገራቸው ተመለሱ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 21፣ 2013 ― 100 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈተው ወደ አገራቸው ተመለሱ ታንዛኒያን አቋርጦ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚደረግ ህገ ወጥ ጉዞ በታንዛንያ መንግስት በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የሆኑ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸው ታውቋል።

100 እንደሆኑ የተገመተው ኢትዮጵያውያኑ አቶ አለማየሁ ከተማ በተባሉ ኢትዮጵያዊ እና ኢንጂነር ጃቢር በተባሉ ታንዛኒያዊያ በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦች ሙሉ ወጪ ተሸፍኖላቸው ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በዳሬሰላም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በመታለል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከፍለው እጅግ አደገኛ የሆነ ህገ ወጥ ጉዞ የሚያደርጉ ሲሆን፤ በመንገዳቸው ላይ ለርሃብ፣ ለእስር፣ ለስቃይ ብሎም ለሞት እንደሚዳረጉ ይነገራል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img