Thursday, October 17, 2024
spot_img

በደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ ሕወሓት ተኩሶታል በተባለ የከባድ መሳሪያ ከ30 በላይ ንጹሐን መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 21፣ 2013 ― በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ 4 የገጠር ቀበሌዎች ሕወሓት ተኮሰው ባሉት ከባድ መሳሪያ አንዲትን ነፍሰ ጡር ጨምሮ ሠላሳ የሚሆኑ ሲቪሎች መገደላቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡

አቶ ውለታው ጌራወርቅ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት በወረዳው ጥቃት አድርሷል ያሉት የሕወሓት ቡድን የነዋሪዎችን ቤት ንብረት በከባድ መሳሪያ ድብደባ ማውደሙንና የቤት እንስሳትም መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጤና ጣቢያዎችና የተከማቸ እህል መውደሙን የተናገሩት አስተዳዳሪው፣ በበቀል ስሜት እንስሳት ተመተዋል ሲሉም ተናግረዋል።

በዚሁ ጥቃት ንብረት እና ከብቶቻቸው የተገደሉባቸው የአካባቢው ነዋሪም የተፈጸመውን ለሬድዮ ጣቢያው ሲያስረዱ ተደምጠዋል፡፡ ነዋሪው በደረሰባቸው ወድመት በአሁኑ ወቅት ሌሎች ሰዎች ጋር ተጠግተው እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

ጥቃቱን በማድረስ በአካባቢው አስተዳዳሪና በነዋሪዎች የተወነጀለው በመንግሥት በሽብር የተፈረጀው የሕወሓት ተዋጊዎች ቃል አቀባይ ናቸው የተባሉ ሰው በዚሁ ጣቢያ ቀርበው ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ሠራዊታቸው ‹‹በሲቪሎች ላይ ጉዳት የማያደርስና ከፍተኛ ሥነ ምግባር ያለው ነው›› ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

በሌላ በኩል ቢቢሲ አናገርኳቸው ያላቸው በደቡብ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ የሆኑት አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው እንደተናገሩት ሕወሓት ወደ ደቡብ ጎንደር ዞን በመግባት በተለይ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ጎብጎብ ሳሊህ፣ እንዲሁም ጉና በጌምድር እንዲሁም በከፊል የፋርጣን አካባቢዎችን ተቆጣጥረው ነበር ብለዋል።

በዚህ ወቅትም በአካባቢዎቹ የሚገኙ ሆስፒታሎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋም፣ የመብራት ሰብ ስቴሽን፣ ባንኮችና ሌሎችም ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የግል ንብረቶች ሳይቀሩ መዘረፋቸውን የሚናገሩት አቶ ይርጋ፣ ሌሎች ንብረቶች ደግሞ መልሰው ጥቅም ላይ እንዳውሉ ሆነው ወድመዋል ብለዋል።

ከባድ ውድመትና ዘረፋ ደርሶበታል የተባለው በንፋስ መውጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊታውራሪ ገብርዬ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለምነው ስዩም ባንኩ በሚሊዮኖች ብር የሚገመት ዘረፋና የንብረት ውድመት ደርሶበታል እንዳሉትም የዜና ወኪል አስነብቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img