Thursday, October 17, 2024
spot_img

ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና በሶማሌ ለሐረሪ ተወላጆች የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚቋቋም አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 20፣ 2013 ― ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚኖሩ የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ በተለያዩ ከተሞችና ክልሎች የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚቋቋሙ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ መስከረም 20 ለሚደረገው ምርጫ የምርጫ ጣቢያዎች ይቋቋማሉ ያለው በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች፣ በኦሮሚያ (አዳማ፣ ጭሮ፣ ኮምቦልቻ፣ ጉርሱም፣ ፈዲስ፣ ደደር እና ሃሮማያ) እንዲሁም በሶማሌ ክልል ነው፡፡

ከሐረሪ ክልል ውጭ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የብሔረሰብ ተወላጆች አባላት በሐረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አባላት ምርጫ ላይ መሳተፍ አይችሉም በሚል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ወስኖ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ውሳኔውን በመቃወም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ በሰበር ችሎት መሰረት የብሔረሰቡ ተወላጆች በተለያዩ አካባቢዎች ሆነው መምረጥ እንደሚችሉ ተበይኗል።

ስድስተኛው አጠቃላይ ብሔራዊ ምርጫ በዋናነት ሰኔ 14፣ 2013 የተካሄደ ቢሆንም በጸጥታ ችግር፣ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዩ ግድፈቶች፣ በመራጮች ምዝገባ ላይ በቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ የድምፅ መስጫው ቀን በአንዳንድ ክልልሎችና የምርጫ ክልሎች እንዲራዘም መወሰኑ ይታወቃል።

ምርጫ የተራዘመባቸው ሶማሌ፣ ሐረሪ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምርጫው መስከረም 20 ምርጫ እንዲካሄድ ተወስኗል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img