Thursday, October 17, 2024
spot_img

ኢሰመኮ ወደ አማራ ክልል የመርማሪ ቡድን ሊልክ መሆኑን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 19፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ካለው የትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ የተፈጸመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት መድረስ፣ ግድያ፣ ዘረፋ እና መፈናቀል በተመለከተ ምርመራ ለማካሄድ ወደ አማራ ክልል መርማሪ ቡድን ሊልክ መሆኑን አሳውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ነሐሴ 13፣ 2013 በአማራ ክልል ጎነደር ደብረ ታቦር ከተማ በሕወሃት ታጣቂዎች እንደተፈጸመ በተነገረ የከባድ መሳሪያ ድብደባ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አምስት ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

በተጨማሪም በሟቾቹ ግቢ ተከራይተው ይኖሩ የነበሩ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ገልጧል፡፡

በመስፋፋት እና በመባባስ ላይ የሚገኘው ግጭት በሲቪል ዜጎች ከፍተኛ ጉዳት እና ሰብአዊ ቀውስን በማስከተል ላይ ነው ያለው ኮሚሽኑ፣ በግጭቱ የሚሳተፉ ሁሉም አካላት ሲቪል ሰዎችን ኢላማ እንዳያደርጉ አሳስቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img