Monday, October 7, 2024
spot_img

የመንግስታቱ ድርጅት በግጭት ለተጎዱ በ3 ክልሎች ለሚገኙ ከ9 ሺሕ በላይ አባዎራዎች ድጋፍ አድርጌያለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ማድረጉን ገልጧል፡፡

ላለፉት 8 ወራት በትግራይ ክልል እየተካሄደ የቆየው ግጭት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች መስፋፋቱን የገለጸው ኤጀንሲው፤ አሁን ላይ በአማራ ክልል ደባርቅ ብቻ 40 ሺሕ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ከአከባቢው ባለስለጣናት ለማወቅ መቻሉን ጠቁሟል፡፡

ተፈናቃዮቹ ያሉበት ሁኔታ ከባድ በመሆኑ አስቸኳይ የሆነ ሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ያመለከተው ኤጀንሲው፣ እስካሁን 1ሺሕ 800 ለሚሆኑ አባዎራዎች ድጋፍ መደረጉንም ነው በኢትዮጵያ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኔቨን ክሬቨንኮቪች ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይ ክልል ያለው የእርዳታ ተደራሽነት ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ በክልሉም ሆነ በሌሎች ክልሎች ያለውን የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡

አክለውም ዩኤን ኤች ሲ አር በመቀሌ፣ ሽረ እና አፋር ክልል ለሚገኙ 7 ሺ 750 አባዎራዎች የብርድ ልብስ፣ ባልዲ፣ ሳሙና ፣ የወጥ ቤት ቁሳቁሶች እና የትንኝ መረቦች እርዳታ አድርጓል ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው አሁን በየትምህርት ቤቶች ተጠለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሆኑና እስከ መስከረም አጋማሽ የሚጠናቀቁ አዳዲስ መጠለያ ጣብያዎች እየገነባ መሆኑንም ክሬቨንኮቪች ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img