Wednesday, October 16, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱ ተገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― ሦስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ተደሰ አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ሊያ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺሕ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

በአንድ ቀን ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ገልጸዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሶስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ነው የጠቆሙት፡፡

ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

በተያያዘ መረጃ በአዲስ አበባ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን የመክተብ እቅድ እንዳለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዚህኛው ዙር የሚሰጠው ክትባት ቀደም ሲል ክትባቱን ያልወሰዱ፣ እድሜያቸው 35 ዓመት የሆነ እንዲሁም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው ነዋሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በሥራ ባህርያቸው ተጋላጭ ናቸው ተብለው የተለዩ ከ105 በላይ ለሚሆኑ የመንግሥትና የግል ተቋማት መሆኑንም የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ ማስታወቃቸውን አስተዳደሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል።

ከእነዚህ የተለዩት ተቋማት መካከል የትራንስፖርት ዘርፍ፣ የግልና የመንግሥት ባንኮች፣ የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይገኙበታል ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img