Saturday, November 23, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት በአብዬ ግዛት የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በሌላ ለመተካት መስማማቱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን አብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮችን በሌላ ለመተካት መስማማቱን የአገሩ ሹማምንት መናገራቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር ፍጥጫ ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በአወዛጋቢው የአብዬ ግዛት ውስጥ በሠላም አስከባሪነት የተሰማራው የኢትዮጵያ ሠራዊት በሌላ አገር ጦር እንዲተካ ከሦስት ወራት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መጠየቋ መነገሩ ይታወሳል፡፡

እንደ ሱዳን ትሪቡን ዘገባ ከሆነ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም አል መሕዲ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት ፐርፋይት ኦናንጋ አንያንጋ እና ሌሎች የሰላም አስከባሪው ሹምምንት ጋር ካደረጉት የበይነ መረብ ውይይት በኋላ የመንግስታቱ ድርጅት የኢትዮጵያ ወታደሮች የአብዬ ግዛትን ለቀው እንዲወጡ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

የአብዬ ግዛትን ይለቃሉ የተባሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ ከሥፍራው እንዲወጡ ከስምምነት የተደረሰው በቀጣይ ሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያመለክተው ከ3 ሺሕ 300 በላይ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በድርጅቱ ዕዝ ስር በአብዬ ግዛት ውስጥ ተሰማርተው የሠላም ማስከበር ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img