Sunday, October 6, 2024
spot_img

ቦርዱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ መስከረም 20 እንዲካሄድ ወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጳጉሜ 1፣ 2013 ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የያዘለትን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ በአዲስ ዓመት መስከረም 20 እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምርጫ ቦርድ ለሁለት ጊዜያት ያራዘመው ሕዝበ ውሳኔ፣ በከፋ፣ በዳውሮ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞና የሸካ ዞኖች እንዲሁም የኮንታ ልዩ ወረዳን የሚያሣትፍ ነው፡፡

በሌላ በኩል ሰኔ 14፣ 2013 ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን በተመሳሳይ መስከረም 20፣ 2014 እንዲሆን መወሰኑን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ነሐሴ 13፣ 2013 ምርጫ ባልተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ከፓርቲ ተወካዮቹ ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ምርጫ ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል አስተያየት የሰጡ መኖራቸውን፣ በአንጻሩ ደግሞ ሰኔ 14፣ 2013 የተደረገውም ምርጫ የተደረገው በተመሳሳይ የፀጥታ ችግር በነበረበት ሁኔታ፤ አንጻራዊ ሰላም ያለባቸው አካባቢዎች ተለይተው እንደተካሄደ ጠቅሰው፤ አሁን የሚካሄደው ምርጫም እንደቀደመው ሁሉ የተሻለ ፀጥታ ያለባቸውን አካባቢዎች በመለየት ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ተሰጥቷል መባሉንም ገልጧል፡፡

በመጨረሻም መስከረም 20 ድምፅ አሰጣጡ ይከናወን ያለው ቦርዱ፣ ምርጫው የሚከናወነው በሶማሌ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ክልሎች መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img