Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ሰቆቃ የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለውን እስር፣ ግፍ እና መከራ የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ ተካሂዷል።

“እኔም ለወገኔ ድምፅ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ፣ ሰልፈኞቹ በሳዑዲ በእስር በሚገኙ ሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ላይ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍ እንዲቆም ጠይቀዋል።

ሳዑዲ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመች ያለችው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንድትመልስም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

በሳዑዲ በእስር ላይ 80 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩ የኢቲቪ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img