Sunday, November 24, 2024
spot_img

ሳማንታ ፓወር የሕወሓት ተዋጊዎች ከአማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸኳይ እንዲወጡ አገራቸው ጥሪዋን መቀጠሏን ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― የሕወሓት ታጣቂዎች ከአማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸኳይ እንዲወጡ እና ግጭቱን ከማባባስ እንዲታቀቡ የአሜሪካ መንግስት የሚያደርገውን ጥሪ መቀጠሉን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ገልጸዋል፡፡

የዩ ኤስ ኤድ ዋና አስተዳዳሪዋ ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የሕወሓት ተዋጊዎች ጥቃት በከፈቱባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች ለተፈናቀሉ 136 ሺሕ በላይ ሰዎች ድርጅታቸው ድጋፍ ማድረስ መጀመሩን አስታውቀዋል።

ዋና አስተዳዳሪዋ አክለውም የአሜሪካ መንግስት ሕወሃት ከጠብ አጫሪ ተግባሩ እንዲታቀብ እንዲሁም ከአማራ እና ከአፋር ክልል በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡን እንቀጠለም ነው ያስታወቁት፡፡

የሕወሓት ተዋጊዎች እየፈጸሙት ነው ያሉት ተግባር ግጭትን ከማባባስ እና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ስቃይ ከማራዘም የዘለለ ፋይዳ እንደሌለውም አስተዳደሪዋ ገልጸዋል፡፡

የዩ ኤስ ኤድ ዋና አስተዳዳሪዋ ሳማንታ ፓወር ከሳምንታት በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ማድጋቸው የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img