Thursday, October 17, 2024
spot_img

የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር ማሻሻያ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 15፣ 2013 ― የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር ማሻሻያ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ የግብር ፖሊሲ ዳይሬክተር አቶ ሙላይ ወልዱ ነግረውኛል ብሎ ዛሬ ለኅትመት የበቃው ሪፖርተር አስነብቧል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ በማሻሻያው ማእቀፍ ውስጥ ከሚታዩት መካከል የገቢ ግብር እና የተርንኦቨር ታክስ ይገኙበታል፡፡

ይኸው የግብር መሻሻያ የሚደረገው በዋነኝነት በግብር የሚገኘውን ገቢ ለመጨመር መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ ሆኖም ይህ ማለት ግን በህብረተሰቡ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለመጨመር አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ከግብር ጋር ተያይዞ በሚደረጉ ማሻሻያዎች ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና ተጨማሪ የሥራ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚረዳም አመለክተዋል፡፡

የግብር ማሻሻያው ከዓመት በፊት መጀመሩን ያስታወሱት ሙላይ ወልዱ፣ ነገር ግን የኮሮና ቫይረስ መከሰቱ እንዳዘገየው ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየተሠራበት ነው የተባለውን የግብር ማሻሻያ ለማድረግ የሚካሄደውን ክለሳ ከራሱ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተዋቀረ ኮሚቴ ተቋቁሞ በየሳምንቱ እየተገናኘ እየመከረበት እንደሚገኝበት ነው የተገለጸው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img