Tuesday, October 8, 2024
spot_img

መንግሥት ለብሔራዊ ውይይት እየተሰናዳ መሆኑን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 15፣ 2013 ― መንግሥት ብሔራዊ ውይይት ለማካሄድ እየተሰናዳ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህንኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተርያት ቢልለኔ ሥዩም በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ወር ይካሄዳል የተባለው ብሔራዊ ውይይት በምን መንገድ እንደሚካሄድ የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ በተያዘው ወር ይፋ ይደረጋል ያሉት ቢልለኔ፣ ይህንኑ ለማስፈጸም መዋቅር ተዘርግቶ በትግበራ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

በብሔራዊ ውይይት ላይ እነማን ተሳታፊ እንደሚሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተርያት ቢልለኔ ሥዩም የተናገሩት ነገር የለም፡፡

ከትላንት በስትያ የዓለም የሰብአዊነት ቀንን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ፣ ወቅታዊውን የኢትዮጵያን ጉዳይ አንስተው በጦርነት ተፋላሚ ኃይሎች ለሰላማዊ አማራጮች እና ለንግግር እድል እንዲሰጡ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

በትላንቱ መግለጫ በቀጣይ ወር መንግስት ብሔራዊ ውይይት እንደሚያደርግ የገለጹት ፕሬስ ሴክሬተርያት ቢልለኔ ሥዩም፣ የሚካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመት በፊት የጀመረችው የለውጥ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img