አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 13፣ 2013 ― የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መነጋጋራቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ከጄፌሪ ፌልትማን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የሰብዓዊ ድጋፍ በአፋጣኝና በተቀናጀ መልኩ ለማዳረስ እየተከናወኑ ያሉ እና በቀጣይም የታቀዱ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገናል›› ብለዋል፡፡
አክለውም በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያን ሀሳብና አቋምም አስረድተናል ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ የሚገኙት የአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከዚህ ቀደም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ይታወቃል፡፡