Friday, November 22, 2024
spot_img

በትግራይ የገንዘብ እጥረት፣ የነዳጅ እና የቴሌኮም አገልግሎት አለመኖር የሰብአዊ ርዳታ ማስተጓጎሉን የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 13፣ 2013 ― በትግራይ ክልል በባንኮች ዝግ መሆን ምክንያት የተፈጠረው የገንዘብ እጥረት፣ የነዳጅ እና የቴሌኮም አገልግሎት አለመኖር የሰብአዊ ርዳታ ማስተጓጎሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጧል፡፡

ቢሮው ባወጣው ወቅታዊውን የክልሉን ሁኔታ የተመለከተ ሪፖርት ከጠቀሳቸው አገልግሎቶች በተጨማሪ የአይሲቲ ቁሳቁሶችን ማስገባት አሁንም ክልክል መደረጉን አሳውቋል፡፡

በክልል ያለው ሁኔታ ተለዋዋጭ መሆኑን ያመለከተው ማስተባበሪያ ቢሮው፣ ብቸኛ ነው ባለው የአፋር መተላላፊያ እስከ እሁድ ሐምሌ 9፣ 2013 ድረስ በአንድ ወር ውስጥ 318 ርዳታ የጫኑ መኪኖች ወደ ትግራይ ዘልቀዋል ብሏል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ በክልሉ አሁን ካለው በተሻለ ሁኔታ ርዳታ ለማድረስ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም አገልግሎትን ከመመለስ እንዲሁም የገንዘብ እና ነዳጅ እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ ተጨማሪ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልግ ገልጧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img