Wednesday, October 16, 2024
spot_img

ዐብደላ ሐምዶክ ሱዳን የአልፋሽቃ ግዛትን እንደማትለቅ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖራት እንደምትፈልግ ነገር ግን ከወራት በፊት በወታደሮቿ ቁጥጥር ስር ያስገባችውን ኢትዮጵያ ይገባኛል የምትለውን የአልፋሽቃ ግዛት እንደምትጠብቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ወታደሮቻቸው ከወራት በፊት በቁጥጥራቸው ሥር ያስገቡትን እና ከኢትዮጵያ ጋር የሚወዛገቡበትን የድንበር አካባቢ በመጎብኘት መሠረተ ልማቶችን ከትላንት በስትያ ሰኞ ባስመረቁበት ወቅት ነው።

የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣንት የሆኑት የወታደራዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ በአወዛጋቢው ይዞታ ውስጥ ሱዳን ያስገነባቻቸውን መሠረተ ልማቶችን መመረቃቸውን የአገሩ መገናና ብዙኃን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያና ሱዳን ለረዥም ጊዜያት ሲነጋገሩበት የቆየው ለእርሻ ተስማማዊን የአልፋሽቃ አካባቢ ከዘጠኝ ወራት በፊት የሱዳን ሠራዊት የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን በማስወጣት በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት ግዛቱ ወደነበረበት ተመልሶ ንግግር እንዲካሄድ በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ከሱዳን በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ይዞታውን በማጠናከር የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተገንብተውበታል።

የሱዳን ዜና ወኪል ሱና የአገሪቱ ሽግግር ምክር ቤት መሪ ጄነራል አል ቡርሐን በሥነ ሥርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ቁጥጥር ሥር ቆይቶ ወደ ሱዳን በተካተተው የድንበር አካባቢ መረጋጋትና ደኅንነት እንዲሰፍን እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ዘግቧል።

ጄነራሉ ጨምረውም ሠራዊታቸውና ሕዝቡ ግዛቱ ወደ ሱዳን እንዲመለስ ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸው፤ አካባቢው ለእርሻ ተስማማሚ የሆነ ለም መሬት በመሆኑ እያንዳንዱን ስንዝር መሬት ጠብቀው እንዲያለሙ ጥሪ ማቅረባቸውን ሱና ዘግቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img