Wednesday, October 16, 2024
spot_img

መንግስት ከተያዘው ሳምንት ጀምሮ በሳዑዲ ዐረቢያ የታሰሩ ዜጎቿን ሊያመጣ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― መንግስት በሳምንት ሶስት በረራዎችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማድረግ በተለያዩ ማቆያ ማእከላትና እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎቿን ሊያመጣ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ዜጎቹ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ለሃገራቸው እንዲበቁ እንደሚደረግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

በሳምንት ሶስት በረራዎችን በማድረግ በየሳምንቱ አንድ ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ እንደሚደረግም ነው ኤምባሲው ያስታወቀው፡፡

ዜጎቹን በማስመለስ ሥራው ለሴቶች፣ ለህጻናት፣ ለታማሚዎች እና አረጋውያን ዜጎቻችን ቅድሚያ እንደሚሰጥም ገልጿል።

ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውሰጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑና ከሳምንታት በፊት በርካቶች መመለሳቸው የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img