Monday, September 23, 2024
spot_img

በአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ የቆዩ አራት ጋዜጠኞች በዋስትና ተፈቱ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ ለ49 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት አራት የኢትዮ ፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞች በዋስትና ተፈተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች የ“ኢትዮ ፎረም” አዘጋጁ ያየሰው ሽመልስ እና ባልደረባው አበበ ባዩ፣ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲሁም በሚዲያው በተንታኝነት ይሳተፍ የነበረው ፋኑኤል ክንፉ ናቸው።

የአራቱን ጋዜጠኞች የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ እያንዳንዳቸው ተጠርጣሪዎች አምስት ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው እንዲፈቱ ውሳኔ አሳልፎ የነበረው ከትላንት በስቲያ ሰኞ በዋለው ችሎት ነበር።

የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ የዚያኑ ዕለቱ ከፍለው ቢያጠናቅቁም፤ ተጠርጣሪዎቹ ላለፉት ሁለት ቀናት ሳይፈቱ ቆይተዋል።

ሆኖም በዛሬው ዕለት ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ፤ አራቱን ጋዜጠኞች ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች በእስር ከቆዩበት የአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ የፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ መፈታታቸውን የቀድሞው የ“ሰንደቅ” ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ፋኑኤል ክንፉ ነግሮኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል፡፡

ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች ከረፋዱ አምስት ተኩል ገደማ አዲስ አበባ መግባታቸውንም ተገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img