Sunday, September 22, 2024
spot_img

ከሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― ከሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮች አረጋግጫለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

ሰኔ 12፣ 2013 ሁለተኛ ዙር የውሀ ሙሌቱን ያጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ በአንድ የሀይል ማመንጫ ተርባይን ሀይል እንዲያመነጭ በብርቱ እየተሰራ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ ቀሪ ስራዎችና የሙከራ ጊዜን ጨምሮ ሃይል ማመንጨቱ እስከ ሶስት ወራት ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎቹ ይገምታሉ።

አሁን በግድቡ የተያዘው ውሀ በሁለት ሀይል ማመንጫ ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ሀይልን ለማመንጨት የሚያስችለው እንደሆነ መገለጹ ይታወሳል።

በህዳሴው ግድብ ግንባታ ስፍራ የሀይል ማመንጫ ተርባይን እና ጀነሬተር ተከላዎች እየተከናወኑ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በመጀመርያው የሀይል ማመንጫ ተርባይን በስኬት የኤሌክትሪክ ሀይልን የማመንጨቱ ስራ ከተከናወነ የተቀሩት የሀይል ማመንጫዎችን ወደ ስራ ማስገባትን ቀላል እንደሚያደርገው ባለሞያዎች ያብራራሉ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚኖሩት የሀይል ማመንጫ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይልን የማመንጨት አቅም አላቸው። ይህ ማለት ግን የመጀመርያው ሀይል ማመንጫ 375 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክን ያመነጫል ማለት አይደለም ተብሏል፡፡

የግድቡ የሀይል ማመንጫዎች በሙሉ አቅማቸው የኤሌክትሪክ ሀይልን የሚያመነጩት የግድቡ ቁመት ከባህር ጠላል በላይ 640 ሜትር ላይ ሲደርስና ግድቡ በመሉ አቅሙ ውሀ ሲይዝ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡ የመጀመርያው ሀይል ማመንጫም የህዳሴው ግድብ በደረሰበት ቁመትና በያዘው ውሀ ልክ ሀይልን እንደሚያመነጭ ይጠበቃል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በአዲሱ ዓመት 2014 መግቢያ ላይ ከህዳሴው ግድብ ኤሌክትሪክን ለማመንጨት መርሀ ግብር የነበረ ቢሆንም፣ በአንዳንድ የማጠናቀቂያ ስራዎች መዘግየት ሳቢያ የሳምንታት መዘግየት ተከስቷል።

በከፍተኛ ዓለም አቀፍ ጫና ውስጥ ሆና ሁለተኛውን ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብን ውሀ የሞላችው ኢትዮጵያ፣ ግድቡን በፍጥነት ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ማስገባቷ ዲፕሎማሲያዊ ድል ተደርጎ የሚታይ ስለመሆኑም ዘገባው አክሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img