Wednesday, October 16, 2024
spot_img

አጣዬ ከተማ የጸጥታ ስጋት እንዳለባት ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘው አጣዬ ከተማ፣ አሁንም የጸጥታ ስጋት እንዳለባት የከተማዋ ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ ተናግረዋል።

በተያዘው ዓመት ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ በደረሰ ጥቃት፣ ከ250 ሺሕ በላይ የአጣዬና አካባቢዋ ነዋሪዎችን፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ እንደነበር አይዘነጋም።

የአካባቢው ነዋሪዎችም አሁንም ቁስላቸው ሳይደርቅ አንዳንድ ትንኮሳዎች እየታዩ ነው ሲሉ ከንቲባው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ ትንኮሳዎች እንደሚስተዋሉ የተናገሩት አቶ አገኘሁ፣ የባለፈው አይነት ውድመት እንዳይፈጠር በራሳችን ማድረግ ያለብንን እያደረግን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

አልፎ አልፎ ተኩሶች በማሰማት እና የብሄር ጉዳይ በማንሳት ህብረተሰቡን ለማሸበር መሞከርና መተንኮስ ይዘዋል ብለዋል፡፡

ከአጣዬ ከተማ ተፈናቅሎ የነበረው የአካባቢው ነዋሪ አብዛኛው የተመለሰ ሲሆን፣ ንብረቱን በማጣቱ ግን አሁንም በድህነት ውስጥ እንዳለ መስማቱን ዘገባው አክሏል፡፡

ሱቆችና መሰል የንግድ እንቅስቃሴዎች ባለመኖራቸውም፣ ነዋሪው እርዳታ ለመጠበቅ መገደዱ ተገልጿል።

የጸጥታውን ስጋት በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ የሚችለውን እያደረገ ነው ያሉት ከንቲባው መንግስትም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img