Wednesday, October 16, 2024
spot_img

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ ከጄፍሪ ፌልትማን ጋር ተወያዩ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ከአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከፌልትማን ጋር በነገራቸው ቆይታ የልዩ ምልእክተኛው የጉብኝት ማእቀፍ ውስጥ ቁልፍ አጀንዳ በሆነው የቀጠናዉ ሰላምና ጸጥታ በሚጠናከርበት ሁኔታ መክረዋል፡፡

በቀጠናው የሚስተዋሉ ግጭቶችና የአፈታት ስትራቴጂያቸው ምን መምሰል አለበት የሚለውም ሌላው የመከሩበት ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ ከጁቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ጁቡቲ በየትኛውም የዓለም ክፍል ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን ድጋፍ እጠናክራ እንደምትቀጥልበትም ለፌልትማን አረጋግጠውላቸዋል፡፡

የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኦማር ጊሌ ጁቡቲ የአሜሪካ ታሪካዊ አጋር እንደመሆኗ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ከአሜሪካ ጋር ትሰራለችም ብለዋል፡፡

በአሁን ሰአት ጂቡቲ የሚገኙት ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል።

ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በሶስቱ ሀገራት ለዘጠኝ ቀናት ያክል በሚያደርጉት ቆይታም ከሀገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ተጠቅሷል። ውይይቱም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግናን ማምጣት በሚያስችሉ ዕድሎች የተመለከተ እንደሚሆንም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img