Wednesday, October 16, 2024
spot_img

የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ 500 ሺሕ ዶዝ የኮቪድ ክትባቶችን ለገሰ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― የእንግሊዝ መንግሥት በኮቫክስ ጥምረት በኩል 500 ሺሕ ዶዝ አስታራዜኒካ የኮቪድ ክትባቶችን ለኢትዮጵያ ለግሷል፡፡

ክትባቶቹን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አሌክስ ካሜሮን እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ድጋፉ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስደው ሁለተኛውን ዙር እየተጠባበቁ ላሉ ሰዎች ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

ርክክቡን ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ ለተደረገው ድጋፍ የእንግሊዝ መንግስትን አመስግነዋል፡፡ አክለውም ክትባቱ እድሜያቸው ከ35 በላይ ለሚሆኑት ይሰጣል ያሉ ዶክተር ሊያ፣ ተጓዳኝ ሕመም ላለባቸው ደግሞ ከ18 ዓመት በታች ላሉትም እንደሚሰጥ ነው የገለጹት፡፡

በርክክቡ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር አሌክስ ካሜሮን የእንግሊዝ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ዐጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img