Friday, November 22, 2024
spot_img

ሕንድ ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር የመፍታቱ ኃላፊነት የራሷ መሆኑን ገለጸች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 10፣ 2013 ― ኢትዮጵያውያን የገጠሟቸውን ችግሮች የመፍታቱ ኃላፊነት የራሳቸው መሆኑን እንደምታምን ሕንድ አስታወቀች፡፡

በኢትዮጵያ የሕንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ ልክ እንደማንኛውም ሉዓላዊ ሀገር ሁሉ ኢትዮጵያም የገጠማትንና የሚገጥማትን ችግር የመፍታቱ ኃላፊነት የራሷ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ፤ የተሻለውን የማድረግ እና የወደፊቱን የመወሰን ስልጣን በራሷ እጅ ላይ ያለ መሆኑንም አምባሳደሩ አንስተዋል። ሕንድ ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር በራሷ እንደምትፈታው ሙሉ እምነት እንዳላት ተናግረዋል።

ሕንድ ከብሪታኒያ ቅኝ አገዛዝ ነጻነቷን የተቀዳጀችበት 75 ዓመት አዲስ አበባ በሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ ተከብሯል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ ስለሕንድ እና ኢትዮጵያ ወዳጅነት የተጠየቁት ዲፕሎማቱ፤ አዲስ አበባ እና ኒውዴልሂ ያላቸውን ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ፤ ሕንድ ነጻነቷን እ.አ.አ በ1947 ባገኘች ማግስት የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመረች ቀዳሚ ሀገር መሆኗንም ዲፕሎማቱ ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያለው ችግርም በራሳቸው በኢትዮጵያውያን አቅም እንደሚፈታም ያነሱት ዲፕሎማቱ ሁሉንም ነገር በኢትዮጵያውን የሚፈታ መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለውን ግድብ በተመለከተ አስተያየት የሰጡት አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ፤ ዓባይ ወንዝ በኢትዮጵያ፤ ናይል ደግሞ በሱዳን እና ግብጽ ለዘመናት መኖሩ የሚታወቅ እንደሆነ አንስተዋል።

በወንዙ ዳርቻ ላይ ሰዎች በሰላም ሲኖሩ እንደነበር የገለጹት አምባሳደሩ፤ በግድቡ ዙሪያ አለመግባባት ውስጥ የገቡት ሶስቱ ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደርጋቸው መልኩ ችግሮችን እንዲፈቱም ጠይቀዋል፡፡

ሕንድ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላት ገልጸው በግድቡ ዙሪያ ያላግባባ ያለ ነገር ካለ ሶስቱም ቁጭ ብለው ሊፈቱ እንደሚገባ ገልጸዋል መባሉን የዘገበው አል ዐይን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img