Sunday, September 22, 2024
spot_img

ኤምቲኤን በሁለተኛው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ላይ አይሳተፍም ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 8፣ 2013 ― በመጀመሪያው የኢትዮጵያ የቴሌኮም ጨረታ 600 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ ማሸነፍ ያልቻለው የደቡብ አፍሪካው ኤምቲኤን በሁለተኛው የቴሌኮም ፈቃድ ጨረታ ላይ አይሳተፍም ተብሏል፡፡

ኤምቲኤን በጨረታው የማይሳተፈው በወቅታዊ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ ስጋት ስለገባው መሆኑን ዘ ኢስት አፍሪካን አስነብቧል፡፡

ሁተኛውን ጨረታ አስመልክቶ በቅርቡ ለሚዲያዎች የተናገሩት የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ለጨረታው የሚያቀርቡትን ዋጋ ለማሳደግ አንዳንድ ለውጦች መደረጉን ገልጸው ነበር፡፡

የኤምቲኤን ግሩፕ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ራልፍ ሙፒታ በግንቦት ወር መጨረሻ ለተቋሙ ባለድርሻዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በጨረታው ላይ ለውጦችን ካደረገ በጨረታው ለመሳተፍ እንደሚያጤኑ ገልጸው ነበር፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ቢደረግ ብለው ከጠቀሱት መካከል የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ነበረበት፡፡

የኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ በሁለተኛው ጨረታ ባለስልጣኑ ከሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች መካከል የኤምቲኤን ሥራ አስፈጻሚ የጠቀሱት የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት ቢካተትም ኩባንያው ከተሳትፎ ታቅቧል፡፡

በኢትዮጵያ የቴሌኮም ጨረታ የመጀመሪያው ዙር የተለያዩ ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የተባለው ተቋም ከፍተኛውን 850 ሚሊዮን ዶላር በማቅረብ በጨረታው አሸናፊ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img