Friday, November 22, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ሁኔታ እንደሚመቻች የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁበት ሁኔታ እንደሚመቻች የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ አስታውቀዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ከሆነ ባለፉት ጊዜያት ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በድምሩ 10 ሺሕ 164 ተማሪዎችን ማስወጣት ተችሏል፡፡

ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በ2013 የትምህርት ዘመን ከአዲግራት፣ አክሱም እና መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተማራቂ ለነበሩ ነገር ግን ያልተጠናቀቁ የትምህርት ተግባራት ያሏቸው ተማሪዎች በቀጣይ በሚቀመጥ አቅጣጫ መሠረት የሚመረቁበት መነግድ እንደሚኖር አሳውቀዋል፡፡ ለዚህም ተማሪዎች በትእግስት እንዲጠባበቁ ነው የጠየቁት፡፡

በሌላ በኩል ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተሰባስበው በነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የክረምት ትምህርት ለመከታተል በጸጥታ ችግር ወደ አካባቢው መጓዝ ያልቻሉም የሚማሩበት ሁኔታ ስለሚመቻች በትእግስት እንዲጠብቁ ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img