Sunday, September 22, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ነዋሪዎች የኮቪድ ክትባት መውሰድ ይችላሉ ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― በመላ አገሪቱ የኮቪድ-19 ክትባት የሚሰጣቸው ዜጎች የዕድሜ ገደብ ዝቅ ከመደረጉ በተጨማሪ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲካተቱ መደረጉ ተገልጧል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገሪቱ በአሁኑ ወቅት ስላለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የክትባት አቅርቦትን በተመለከተ እንደተናገሩት በሽታው እየተስፋፋ መሆኑንና ለዚህም የክትባቱ ተደራሽነት ላይ ለውጥ መደረጉን አመልክተዋል።

በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ የኮሮና ቫይረስ ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ሲጀምር የጤና ሚኒስቴር ክትባቱ በቀዳሚነት ለጤና ባለሙያዎች፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ50 እስከ 60 ሆኖ ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው እንዲሰጥ መመሪያ አውጥቶ ነበር።

በአገሪቱ የወረርሽኙ መከላከያ ክትባት መሰጠት ከጀመረ ከስድስት ወራት በኋላ ግን ክትባቱን በቅድሚያ ማግኘት ያላባቸው ሰዎች የዕድሜና የጤና ሁኔታ ላይ ለውጥ መደረጉ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ከሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በተለየ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋባት በመዲናዋ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደር እድሜያቸዉ ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች እንደሚሰጥ የጤና ሚኒስተሯ ተናግረዋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረሽኝ ምጣኔ በአንጻራዊ ሁኔታ ቀደም ሲል ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቶ እንደነበር ሚኒስትሯ አስታውሰው፤ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ግን የበሽታው መስፋፋትና የጉዳት መጠን መጨመሩን ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img