Tuesday, October 15, 2024
spot_img

ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ላይ ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል አጋጠመ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ በመባል በሚታወቀው አካባቢ ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል ማጋጠሙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የድንጋይ መንሸራተት ናዳው ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ገልጧል፡፡

ይህን ችግር በቶሎ ለመቅረፍም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል በመላክ በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑን ገልጿል።

ስራው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት ሲደረግ የሚያሳውቅ መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img