Tuesday, October 15, 2024
spot_img

አሜሪካ ጄፍሪ ፌልትማንን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 7፣ 2013 ― የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አድርገው የሾሟቸው ጄፍሪ ፌልትማንን በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ሊልኩ ነው፡፡

የፕሬዝዳንት ባይደን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጃኪ ሱሊቫን በትዊተር ገጻቸው ላይ ‹‹በዚህ ወሳኝ ወቅት ፕሬዝዳንቱ ልዩ መልዕክተኛ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ጥያቄ አቅርበውላቸዋል›› ሲሉ አስፍረዋል፡፡

‹‹ለወራት የዘለቀው ጦርነት በታላቋ ሀገር ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና ክፍፍል አምጥቷል። ይህ ሁኔታ በተጨማሪ ውጊያ አይሽርም›› ያሉት ሱሊቫን፣ የጦርነቱ ተፋላሚ ወገኖች ‹‹ወደ ድርድር ጠረጴዛ በአስቸኳይ እንዲመጡ›› ጥሪ አቅርበዋል።

ይህንኑ የባይደንን አማካሪ መልዕክት ከቀናት በፊት ኢትዮጵያ የነበሩት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገጻቸው ላይ አስተጋብተውታል።

መልዕክቱን ‹‹አስቸኳይ›› ሲሉ የጠሩት ሳማንታ ፓወር፣ ‹‹ለዚህ ግጭት ወታደራዊ መፍትሔ የለም›› ሲሉ በትግራይ ያለው ቀውስ ሊፈታ የሚችለው በድርድር መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፈው ግንቦት መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ የነበሩት ጄፍሪ ፌልትማን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img