Friday, November 22, 2024
spot_img

በኦሮሚያ ክልል ከ400 ሺሕ ሕዝብ በላይ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 6፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ለረዥም ጊዜ በቆየ የዝናብ እጥረት ሰበብ ከ400 ሺሕ በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት መጋለጡ ተነግሯል፡፡

የምግብ እጥረቱ ያጋጠመው በዞኑ በሚገኙት ሻላ፣ ሲራሮ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ እና ወንዶ ተብለው በሚጠሩ አምስት ወረዳዎች ውስጥ ነው።

የምዕራብ አርሲ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊ አቶ ያሲን ጋርጁ ነግረውኛል ብሎ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ በዞኑ የበጋ ወቅት በመርዘሙ እህል ሳይዘራ በመዘግየቱ የምግብ እጥረቱ ሊያጋጥም ችሏል።

ኃላፊው ከአምስቱ ወረዳዎች በሁለቱ ማለትም በሻላ እና ሲራሮ ከምግብ እጥረት በተጨማሪ የውሃ እጥረት መኖሩንም የተናገሩ ሲሆን፣ የምግብ እጥረት ካጋጠማቸው ሰዎች መካከል የተወሰኑት ከዚህ ቀደምም ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበር አስረድተዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኃላፊው አቶ ያሲን ጋርጁ የምግብ እጥረቱ ይከሰት እንጂ በምግብ እጥረቱ ሳቢያ እስካሁን ሕይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አለመደረጉን ይናገራሉ።

ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እና በምግብ እጥረቱ የሰው ሕይወት እንዳያልፍ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ከክልል እና ከፌደራል መንግሥት ጋር እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img