Tuesday, October 15, 2024
spot_img

ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዙ በነበሩ ተሸከርካሪዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ 7 ሰዎች ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― በአማራ ክልል ከምትገኘው ቻግኒ ከተማ ተነስተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተማ ወደ ሆነችው ግልገል በለስ ሲጓዙ በነበሩ ሁለት የህዝብ ማመላሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪዎች ላይ በትላንትናው ዕለት በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል፡፡

ይህንኑ የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ዋና አስተባባሪ የሆኑት ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ እንዳረጋገጡለት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል፡፡

በተሽከርካሪዎቹ ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው በማንዱራ ወረዳ መግቢያ ገነተ ማሪያም ከተማ ጅግዳ ስላሴ አካባቢ ትላንት ማክሰኞ ነሐሴ 4፤ 2013 ከቀትር በኋላ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በጥቃቱ የተገደሉ የሰባት ሰዎች አስክሬን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ወደ ፓዌ አጠቃላይ ሆስፒታል አስክሬን ክፍል መግባቱን አንድ የሆስፒታሉ ሰራተኛ መናገሩን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ጥቃቱ መፈጸሙን ያረጋገጡት ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ፤ የደረሰውን የጉዳት መጠን በተመለከተ ግን “ዝርዝር መረጃ የለኝም” ብለዋል። ጥቃት ወደ ተፈጸመበት ቦታ “ክትትል ሊያደርግ የወጣ አጠቃላይ ሰራዊት አልተመለሰም” ሲሉም አክለዋል። ሌተናል ጄነራል አስራት “አደጋ ካደረሰው ኃይል ጋር ግጭቶች ነበሩ” ቢሉም፤ የጥቃት ፈጻሚዎቹን ማንነት ሳይገልጹ አልፈዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ጥቃቱን የፈጸሙት የተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ከግልገል በለስ ማንዱራ ያለውን መንገድ ሲጠብቁ የነበሩ ታጣቂዎች ናቸው ባይ ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img