Sunday, October 6, 2024
spot_img

በርሊን ኤምባሲ የሚሠሩ ስድስት የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጠቅልለው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ መታዘዛቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 5፣ 2013 ― በጀርመን በርሊን ኤምባሲ የሚሠሩ ስድስት የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጠቅልለው ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ መታዘዛቸው ተሰምቷል፡፡

በኤምባሲው ውስጥ ከሚገኙት ውስጥ በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ውጭ እነዚህ ስድስት ዲፕሎማች እንዲመለሱ የታዘዙት ከነ ቤተሰቦቻቸው መሆኑን የኤፍ አይ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል በዚያው በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንፅላ ሙሉ ለሙሉ እንደተዘጋም ነው የተነገረው፡፡

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሌሎች በርካታ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም በተመሳሳይ እንደተዘጉ ሲነገር፣ ለመዘጋታቸው ዋነኛው ምክንያት መንግስት ከምእራባውያን ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ ደሞዝ መክፈል በመቸገሩ እንደሆነም ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ፡፡

በሌላ መረጃ በአሜሪካ ዋሺንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሥራ አቁሟል የሚል መረጃ እየተሰራጨ ቢሆንም፣ የሚወራው ሐሰት መሆኑን እወቁት ሲሉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ የአምባሳደሩ ማስተባበያ የመጣው ከሰሞኑ በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ ኤምባሲው ሥራ ማቆሙን የሚያመለክቱ መረጃዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በተያዘው ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መዝጊያ እለት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ኤምባሲዎቿ መካከል ግማሽ ያህሉን ልትዘጋ እንደምትችል መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img