Monday, October 14, 2024
spot_img

የኢትዮጵያዊ ቤተሰብን የትምህርት ጉዞ የሚያሳይ ፎቶ በኧርዝ ፎቶ ውድድር አሸናፊ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― በኢትዮጵያ አንድ ቤተሰብ በትምህርት የደረሰበትን ጉዞ የሚያሳይ ፕሮጀክት የዘንድሮው ‘ኧርዝ ፎቶ’ ውድድር አሸናፊ ሆኗል።

በዚህ ውድድር ላይ አሸናፊ የሆነችው ሮዚ ሃላም የተባለችው የፎቶ ባለሙያ በአንድ ፍሬም ላይ ሦስት ፎቶዎችን በማሳየት የመማር መብትን ታስቃኛለች።

በፎቶው ላይ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የግብርና ኑሮም ነው ከሚተዳደር ቤተሰብ የወጣችውና የትምህርት መመዝገቢያ ዕድሜዋ ካለፈ በኋላ ትምህርት ቤት የገባችው ሰላማው በዋነኝነት ትታያለች፡፡

እነዚህ ፎቶዎች ‘ፒፕል’ በተሰኘው ዘርፍ አሸናፊ ሆነዋል።

‹‹ትምህርት መሠረታዊ የሰው ልጅ መብት እና ብልህ ኢንቨስትመንት ነው›› ያለችው በፎቶው ያሸነፈችው ሃላም፣ ‹‹ለልማት ወሳኝ እና ለማህበራዊ ደህንነት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ደህንነት፣ ለጾታ እኩልነት እና ለሰላም መሠረቶችን ለመጣል ይረዳል›› ስትል አስረድታለች፡፡

የእንግሊዝ ፎረስትሪ ድርጅትና ሮያል ጂኦግራፊካል ሶሳይቲ 55 ፎቶግራፎች እና ከአራት ፊልሞች ዝርዝር ውስጥ በስድስት ምድቦች አሸናፊዎቹን መርጠዋል።

በዚህ ውድድር ላይ ዕጩ የሆኑት ፎቶዎች በኧርዝ ፎቶ አውደ ርዕይ ለሁለት ሳምንታት ያህል ለንደን በሚገኘው ሮያል ጂኦግራፊካል ሶሳይቲ ፓቭልዮን ውስጥ ለዕይታ ይቀርባሉ የተባለ ሲሆን፣ ከዚህ ተጨማሪም የተመረጡ ፎቶዎች በእንግሊዝ ፎረስትሪና ፎረስትስ ለዕይታ እንደሚቀርቡ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img