Saturday, November 23, 2024
spot_img

ዶክተር ደብረጽዮን ለፌዴራል መንግሥት አለው ያሉትን አማራጭ አቀረቡ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 4፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሓት አመራር የሆኑት ዶክትር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለፌዴራል መንግሥት ሁለት አማራጮች ብቻ ናቸው ያሉት ያሉት ብለዋል፡፡

በሕወሓት የክልሉ ፕሬዝዳንት ተብለው የሚጠሩት ዶክተር ደብረጽዮን በትግራይ ቴሌቪዥን ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ የፌዴራል መንግሥት ያለው አማራጭ በትግራይ ክልል ‹‹ቀረበለት›› ያሉትን ቅድመ ሁኔታ ‹‹ተቀብሎ መደራደር ካልሆነ ግን እንደመስሰዋለን›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል እጣ ፋንታ ላይ ስለመወሰን የተናገሩት ዶክተር ደብረጽዮን፣ ገና ጦርነት ላይ ስለሆንን፣ ‹‹ሄዶ ሄዶ ጦርነቱ ሲገባደድ የሚፈጸም ነው›› ብለዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ሕወሓት በአሁኑ ወቅት እያደረገ ነው ያለው ትንኮሳ ‹‹ትዕግስት የሚፈታተንና እስካሁን በተገበረው የተናጠል የተኩስ አቁም ምክንያት የተከተለውን የመከላከል አቋም ለመለወጥ የሚያስገድድ›› መሆኑን ገልጧል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በወጣው መግለጫ ምንም እንኳ መንግስት በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መጠነ ሰፊ ጥረት ያደረገ ቢሆንም፣ ሕወሓት ግን ‹‹ግጭቱን ወደ ጎረቤት ክልሎች በማስፋፋት አገሪቱ እንዳትረጋጋ በማድረግ ላይ›› እንደሚገኝ አሳውቆ ነበር፡፡

በመሆኑም ‹‹መንግስት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደጎን በመተው በሽብር ተግባሩ ላይ ተጠምዶ የሚገኘውን›› እኩይ ሲል የጠራውን የሕወሓት ቡድን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያወግዘው ጥሪውን› አቅርቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img