Monday, November 25, 2024
spot_img

የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት አቶ ታምራት ነገራ ላይ ክስ ለመመስረት ክትትል ላይ ነኝ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ሐምሌ 12፣ 2013 ― የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሰጪ በሆኑት አቶ ታምራት ነገራ ላይ ክስ ለመመስረት ክትትል ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ይህን ያስታወቀው “የአሃዳዊያን ተላላኪ የሆኑ ግለሰቦችና ሚዲያዎች በጭፍን ጥላቻ ተነሳስተው በተደጋጋሚ በሚያሰራጩት መልዕክት በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ለማድረግ ክትትል እያደረገ” መሆኑን ባመለከተበት መግለጫው ነው።

ቢሮው በመግለጫው “ተራራ በሚባል ሚድያ አቶ ታምራት ነገራ የተባለ አሃዳዊ ስርአት ናፋቂ ያስተላለፈው መልዕክት ህዝባችንን የማይገልጽና በጭፍን ጥላቻ ተነሳስቶ ያሰራጨው ከንቱ ጩኸት መሆኑን ህዝባችን መረዳት ይኖርበታል” ያለ ሲሆን፣ አቶ ታምራት ላይ ክትትል የሚያደርገው በየትኛው ንግግራቸው መሆኑን የጠቀሰው ነገር የለም።

ሆኖም “ግለሰቡን በህግ እንዲጠየቅ ለማድረግ የሚደረገው ክትትል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ አንዳለ ሆኖ ህዝባችን ለቁራ ጩኸትና ለእንቶ ፈንቶ አጀንዳቸው ትኩረት መስጠት እንደሌለበት” ገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img