Monday, October 14, 2024
spot_img

ሕወሃት ሕፃናትን ለውትድርና አሰልጥኗል በሚል የወጡ መረጃዎችን አስተባበለ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ ሐምሌ 11፣ 2013 ― ሕወሃት ከሰሞኑ ሕጻናትን ውትድርና አሰልጥኗል በሚል ሲቀርብበት የቆየውን መረጃ አስተባበሏል፡፡ ቡድኑ ‹‹የትግራይ ክልላዊ መንግሥት›› በሚል ባወጣው መግለጫ አንድም እድሜው ለውትድርና ያልደረሰ ሰው አላሰለጠንኩም ብሏል፡፡

ሕወሃት ሕፃናትን ለውትድርና አሰልጥኗል ለሚለው ክስ መነሻ ነው ያለውን የአሜሪካው ኒውዮርክ ታይምስ ይዞት የወጣውን ዘገባ አስመልክቶ መልስ የሰጠ ሲሆን፣ በሚዲያው ምስላቸው የታዩ ሕጻናት ወታደሮቼ ሳይሆኑ የፌዴራል መንግሥቱን ወታደሮች በማሸነፌ ደስታቸውን ሲገልጹ የነበሩ ናቸው ነው ያለው፡፡

በተመሳሳይ ለአሶሽየትድ ፕረስ ቃለ ምልልስ ሰጥታለች ያላትን ታዳጊ አስመልክቶም ምኞችዋን የገለጸችው እንጂ የኔ ወታደር አይደለችም ሲል ገልጧል፡፡

አክሎም ሕፃናትን ለውትድርና እንዳልመለመልኩ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲያረጋግጥልኝ፣ ጋዜጠኞች፣ የረድኤት ተቋማት እና ሌሎች ታዛቢዎች በማሰልጠኛ ማእከል መጥተው መታዘብ ይችላሉ ሲል አጠቃሏል፡፡

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት ላይ የሰነበተው ሕወሃት በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት እንደተፈረጀ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img