Monday, October 14, 2024
spot_img

አምነስቲ የተጠቀመው ፎቶ ግራፍ ተቃውሞ አስተናገደ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ሐምሌ 10፣ 2013 ― ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሁለት ቀናት በፊት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ያያዘው ፎቶ ግራፍ ተቃውሞ አስነስቶበታል፡፡

አምነስቲ ባወጣው የትግራይ ተወላጆች እስርን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ላይ ባያያዘው ፎቶግራፍ በሰልፍ የቆሙ ሰዎች በፖሊስ ፍትሻ ሲደረግባቸው የሚያሳይ ሲሆን፣ ተቃሞውን ያቀረበው የፎቶው ባለመብት መሆኑን የገለጸው አማኑኤል ስለሺ የተባለ የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ የፎቶ ጋዜጠኛ ነው፡፡

የፎቶ ጋዜጠኛው አማኑኤል ፎቶግራፉን ያስቀረው ባለፈው ወር አጋማሽ በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ወቅት መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመግባታቸው በፊት በነበረ ፍተሻ ወቅት መሆኑን ነው ያመለከተው፡፡

አማኑኤል ስለሺ አምነስቲ ያያዘውን ፎቶ እንዲወረድ የጠየቀ ቢሆንም፣ ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ሰአት ድረስ ከሪፖርቱ ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡

አምነስቲ የተጠቀመው ከሪፖርቱ ጋር ግንኙነት የሌለው ፎቶ ግራፉ የተለያዩ አስተያየቶች የተሰጡበት ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን በባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ድርጅቱ ይህን ያደረገው ለታላቋ ኢትዮጵያ ባለው ጥላቻ ነው ሲሉ ተችተውታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img