Monday, November 25, 2024
spot_img

ዋትስአፕ ደንበኞቹ ያለ ስልክ መልዕክት እንዲላላኩ ሊያስችል ነው

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ሐምሌ 9፣ 2013 ― ዋትስአፕ ለመጀመሪያ ግዜ ተገልጋዮቹች ስልካቸውን ሳይጠቀሙ መልዕክት እንዲለዋወጡ የሚያስችል ዘዴ ተገባራዊ ለማድረግ ሙከራ ጀመረ።

በአሁኑ ወቅት ዋትስአፕን በዴስክቶፕ መተግበሪያ አልያም በድረ-ገጹ ላይ ለመጠቀም ግዴታ ደንበኞች በስልካቸው ላይ ያለው የዋትስአፕ መተግበሪያ ከኢንተርኔት መገናኘት እና መልዕክት መቀበል መቻል አለበት።

ነገር ግን አዲሱ ስርዓት ተጠቃሚዎች ስልካቸው ባትሪ ጨርሶም መልዕክቶችን እንዲልኩ እና እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል፡፡

እንደ ኮምፒዮተር እና ታብሌት ያሉ እስከ አራት የሚደርሱ ሌሎች መሳሪያዎች በአንድ ጊዜ አብረው ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ብሏል ዋትስአፕ።

አገልግሎቱ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ይፋ ከመደረጉ በፊት ለሙከራ አሰራሩ ለተወሰነ ቡድን ይለቀቃል። በሂደትም አፈፃፀሙን ለማሻሻል እና ማስተካከያዎች ለመጨመር ታቅዷል።

ከሁለት ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ዋትስአፕ ‘ከላኪው እስከ ተቀባዩ’ ድረስ የሚላኩ መልዕክቶች በሚስጥር የሚጠበቁ ናቸው ማለቱ መተግበሪያውን ተመራጭ ያደረገው ሲሆን፣ አሁንም በአዲሱ ስርዓት ይህ አሰራር እንደሚቀጥል ዋትስአፕ ማስታወቁን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img