አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ሐምሌ 7፣ 2013 ― በጃኬን አሳታሚ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ስር የሚንቀሳቀሰው አዲስ ስታንዳርድ ድረ ገጽ ሥራ ማቆሙን አሳወቀ።
ድረ ገጹ ሥራውን ያቆመው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፍቃዱ ስለተነጠቀ መሆኑን ባወጣው አጭር መግለጫ አስታውቋል።
እንደ ሚዲያው ከሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለምን ፍቃዱን እንደነጠቀው ማብራሪያ አልሰጠም።
በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ይህ ዘገባ እስከተሰናዳበት ሰአት ድረስ ያለው ነገር የለም።