Monday, October 14, 2024
spot_img

የኦሮሚያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መዝመታቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 8፣ 2013 ― የኦሮሚያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መዝመታቸውን የመንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

ከልዩ ኃይሎቹ መካከል ቀድሞ መደ ሰሜን መድረሱ የተነገረው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ሲሆን፣ የሲዳማ ልዩ ኃይልም በተመሳሳይ መድረሱን የኢቲቪ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የሀገርን ሰላም ለማስከበር ተንቀሳቅሷል የተባለው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ሥፍራው መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንም አረጋግጧል፡፡

ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ሕወሃት ግዛት ለማስመለስ አድርጎታል በተባለ ጦርነት አላማጣ እና ኮረምን መያዙን ማሳወቁ ይነገራል፡፡

ይህንኑ በተመለከተ በሕወሃት ጦርነት ተከፍቶብኛል ያለው የአማራ ክልል መንግሥት፣ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አብረውኝ ይሰለፉ ማለቱም አይዘነጋም፡፡

በትላንትናው እለት መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‹‹አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም›› ያሉት ሕወሃት፣ ‹‹ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ›› እንደሚገኝና ‹‹የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል›› ብለው ነበር፡፡

በተመሳሳይ የመከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ኃላፊው ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ፣ ‹‹የተናጠል የተኩስ አቁም የመንግሥት ውሳኔ ለሕወሃት እድል ስለሰጠ ያን ለመደምሰስ ሰራዊቱ እየሰራበት ነው›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img