አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ሐምሌ 8፣ 2013 ― የሕወሃት አመራሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከረዥም ጊዜ በኋላ በአማርኛ ቋንቋ በሰጡትና በአሜሪካ ድምጽ በተላለፈ ድምጽ ‹‹የትግራይ ሕዝብ፤ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ዶ/ር ደብረጽዮን በተለየ ሁኔታ ያነሱት ከአማራ ሕዝብ ጋር በተገናኘ ‹‹የትግራይ ሕዝብ ትላንት የአማራ ጠላት አልነበረም፣ ዛሬም የአማራ ጠላት አይደለም፣ ነገም የአማራ ሕዝብ ጠላት አይሆንም›› ብለዋል። ይሁን እንጂ በሥልጣን ላይ ያሉት የዐማራን ሕዝብ ሥልጣናቸውን ላለመልቀቅ የአማራን ሕዝብ ወደ ከፍተኛ ጠፋት እያስገቡት ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡
በሌላ በኩል ሌሎች ኢትዮጵያውን በትግራይ ሕዝብ ላይ ደርሷል ላሉት ጥፋት ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ ወደ ሕግ ይቅረቡ ማለት እንደሚገባቸው ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ደብረጽዮን ‹‹የትግራይን መሬትን ወረው የያዙ ኃይሎች በአስቸኳይ ይውጡ ካልሆነ ግን ባለፉት ስምንት ወራት እንዳደረግነው ሁሉ ታግለን መብታችንን እናስከብራለን›› ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡